Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የጀርመን መንግስት በትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 21፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የጀርመን መንግስት በትምህርትና ስልጠና ዘርፍ ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታወቀ።

የትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ስቴፈን አውርን ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

አምባሳደሩ በትምህርት እና ስልጠና ዘርፍ የጀርመን መንግስት ሲያደርግ የነበረውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

በተለይም በትምህርት ፍኖተ ካርታ ላይ የተቀመጠውን የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ላይ ሰርዓተ ትምህርት ዝግጅት እና ትግበራ ለማጠናከር በሚያስችሉ ቀጣይ ስራዎች ላይ ድጋፍ ለማድረግ በሚያስችል ሁኔታ ላይም መክረዋል።

አምባሳደሩ በቀጣይ የስራ ዘመናቸው ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በቅርበት ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።

የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያ ከጀርመን ብዙ ልምዶችን እና ድጋፎችን እንደምትፈልግ በመግለፅ፤ ለአምባሳደሩ መልካም የስራ ዘመን መመኘታቸውን ከትምህርቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

Exit mobile version