አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፓኪስታን ታይሞር ዔር የተሰኘ ክሩዝ ሚሳኤል በተሳካ መንገድ መሞከሯ ተነገረ፡፡
ኢስላማባድ የሞከረችው ክሩዝ ሚሳዔል የጦር መርከቦች ላይ ከረጅም ርቀት ለማነጣጠር የተነደፈ የላቀ ፀረ-መርከቦች መሣሪያ መሆኑን የተገለጸ ሲሆን፤ የባህር ላይ ደህንነቷን የሚያስጠብቅ እንደሆነም ተገልጿል።
መሳሪያው የተሻለ የባህር ላይ ጥቃት የማከናወን አቅምን የያዘ መሆኑ ተገልጿል።
የፓኪስታን ባህር ኃይል ያስወነጨፈው ታይሞር ክሩዝ ሚሳኤል በባህር ላይ የተመሰረቱ ስጋቶችን የመለየት፣ የመሳተፍ እና ስጋቶችን የማስወገድ አቅሙ ከፍተኛ መሆኑ መነገሩን አናዶሉ ዘግቧል።
የክሩዝ ሚሳኤሉ የተሳካ ሙከራ የፓኪስታንን የመከላከያ አቅም የሚያሳድግ ሲሆን፤ ይህ ወታደራዊ እድገት የሀገሪቱን የውሃ ላይ ደህንነት የሚረጋግጥ ነው ተብሏል፡፡
የፓኪስታን የፖለቲካ እና ወታደራዊ አመራሮች በክሩዝ ሚሳኤሉ ስራ ላይ የተሳተፉ ሳይንትስቶች እና መሃንዲሶችን አድንቀው፤ ውጤቱ ሀገር በቀል የመከላከያ ስርዓት ለሀገሪቱ ቁልፍ አቅም መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በአቤል ነዋይ

