አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ28ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር ቅዱስ ጊዮርጊስ አዳማ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል፡፡
ቀን 9 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የቅዱስ ጊዮርጊስን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ፍፁም ጥላሁን በሁለተኛው አጋማሽ አስቆጥሯል፡፡
ውጤቱን ተከትሎ ቅዱስ ጊዮርጊስ በ35 ነጥብ 10ኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ አዳማ ከተማ በበኩሉ በ33 ነጥብ 14ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
አዳማ ከተማ በሊጉ ተከታታይ ስድስተኛ ሽንፈት አስተናግዷል፡፡

