አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአውሮፓ ህብረት ለማሊ ወታደሮችና ፖሊስ ኃይል ሲሰጥ የነበረውን ስልጠና ማቋረጡን አስታወቀ።
ህብረቱ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው ባለፈው ሳምንት የሀገሪቱን ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ቧባኬር ኬይታ በወታደሮች ከስልጣን መነሳታቸውን ተከትሎ ነው።
የህብረቱ ኃላፊዎች እንደገለጹት ስልጠናው ማሊን የማረጋጋት ዓለም አቀፍ ጥረት አንዱ አካል መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
ለወታደሮችና ፖሊሶች ስልጠና ላይ የተጣለው እግዳ ጊዜያዊ መሆኑንና ዕውቅና ያለው መንግስት ሲመሰረት እንደሚቀጥልም የአውሮፓ ህብረት ገልጸዋል።
እንዲሁም በጎረቤት ኒጀርና ቡርኪናፋሶ የሚሰጠውን ስልጠና እንደሚቀጥል የህብረቱ ኃላፊዎች አስታውቀዋል።
በተጨማሪም 88 አባላት የያዘው የፈረንሳይኛ ተናጋሪዎች ህብረት ማሊን ከአባልነት አግዷል።
ምንጭ፦ አልጀዚራ
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

