Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በኮፐንሀገን ባቡሮች ተጋጭተው ጉዳት ደረሰ 

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በዴንማርክ መዲና ኮፐንሀገን በተከሰተ የባቡር አደጋ 17 ሰዎች መጎዳታቸው ተሰማ፡፡

በሰሜናዊ ኮፐንሀገን በተከሰተው አደጋ ከተጎዱ ሰዎች መካካል አራቱ በአሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ነው የተገለፀው፡፡

የከተማዋ ፖሊስ እንዳስታወቀው÷ ባቡሮቹ የተጋጩት ሂልሮድ እና ካግሩፕ የተባሉ ከተሞችን ከኮፐንሀገን ጋር በሚያገናኘው የባቡር መስመር ላይ ነው።

በተለቀቁ ምስሎችም ሁለቱ ባቡሮች እርስ በርስ ከተጋጩ በኋላ ጉዳት ደርሶባቸው እና ተሰባብረው ታይተዋል፡፡

በአደጋው 17 ሰዎች ጉዳት ሲደርስባቸው ሌሎች ተሳፋሪዎች ግን በሰላም ከባቡሩ መውጣታቸውን አካባቢው የነፍስ አድን ቃል አቀባይ ገልጿል፡፡

በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ተሳፋሪዎች በአካባቢው በሚገኙ ሆስፒታሎች የህክምና አገልግሎት እያገኙ ነው መባሉን ዘገባዎች አመልክተዋል።

በሚኪያስ አየለ

Exit mobile version