Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ምርጫ ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ ወሳኝ ነው – ምሁራን

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ምርጫ ለጠንካራ የፖለቲካ ሥርዓት እና ሀገረ መንግሥት ግንባታ ወሳኝ ነው አሉ ምሁራን፡፡

የጅማ ዩኒቨርሲቲ መምህር ፍቃዱ ቶሎሳ (ዶ/ር) ከፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቆይታ እንዳሉት÷ የመምረጥ መብትን በአግባቡ መጠቀም ቅቡልነት ላለው የፖለቲካ ሥርዓት ግንባታ ሚናው ጉልህ ነው፡፡

በብዙሃን ድምጽ የተመረጠ መንግሥት ቅቡልነት ስለሚኖረው ለሀገር ሰላም፣ ልማትና አንድነት አዎንታዊ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አስረድተዋል፡፡

በፖለቲካ ፖርቲዎች የክርክር መድረክ የሚንሸራሸሩ ለሀገር የሚበጁ ሀሳቦች የጋራ ትርክት እንዲፈጠር በማስቻልና ግጭቶችን በማራቅ ለሀገር ግንባታ መሰረት እንደሚሆኑ ገልጸዋል፡፡

በጅማ ዩኒቨርሲቲ የሕግ መምህርት ሀና ሰቦቃ በበኩላቸው÷የመምረጥ ዴሞክራሲያዊ መብትን በአግባቡ መጠቀም ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ ወሳኝ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

ምርጫው ነጻ፣ ፍትሃዊ እና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ በስኬት እንዲጠናቀቅ ዜጎች በሒደቱ በንቃት መሳተፍ አንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡

ዜጎች በወሰዱት ምርጫ ካርድ የሚፈልጉትን በመምረጥ ለሀገራቸው ዴሞክራሲ መዳበር ያላቸውን ቁርጠኝነት ማሳየት እንዳለባቸውም ምሁራኑ አመልክተዋል፡፡

በወርቅአፈራው ያለው

Exit mobile version