Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ማኅበራዊ ሚዲያ በቅን ልብ ከተጠቀምንበት ሀገር የመገንባት ኃይሉ ከፍተኛ ነው – ኮሚሽነር መላኩ ወልደማርያም

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር መላኩ ወልደማርያም ማኅበራዊ ሚዲያ በቅን ልብ ከተጠቀምንበት ሀገር የመገንባት ኃይሉ ከፍተኛ ነው አሉ።

ምክክር ኮሚሽኑ ከማኅበራዊ ሚዲያ በጎ ተጽዕኖ ፈጣሪ ባለሙያዎች ጋር ተወያይቷል፡፡

ኮሚሽነር መላኩ ወልደማሪያም በውይይቱ ወቅት እንዳሉት፤ በኢትዮጵያ ዘመን የተሻገሩ ችግሮችን ለመፍታት ብቸኛው አማራጭ ምክክር ነው።

የማኅበራዊ ሚዲያ በጎ ተጽዕኖ ፈጣሪ ባለሙያዎች ለሀገራቸው ሲሉ ከኮሚሽኑ ጋር በትብብር እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ማኅበራዊ ሚዲያ ለመልካም ነገር በቅን ልብ ከተጠቀምንበት ሀገር የመገንባት ኃይሉ ከፍተኛ ነው ያሉት ኮሚሽነሩ፤ ሀገራዊ ምክክሩ በሚያልፍባቸው ምዕራፎች በኃላፊነት ስሜት የማኅበረሰቡን ግንዛቤ ማሳደግ ላይ መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡

ከጥቂት ወራት በኋላ በሚደረገው ሀገራዊ  ጉባኤ ላይ ከቅድመ ምክክር ጀምሮ ከኮሚሽኑ ጋር በመተባበር የዜግነት ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም ጠይቀዋል።

በመድረኩ የተሳተፉ ባለሙያዎች ከኮሚሽኑ ጋር በትብብር እንደሚሰሩ ማረጋገጣቸውን የኮሚሽኑ መረጃ አመላክቷል።

Exit mobile version