Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሰኔ 24 እስከ ሐምሌ 17 ድረስ ይሰጣል

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 16፣ 2018 (ኤፍ ኤም) የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በ2018 የትምህርት ዘመን የሚካሄዱ ፈተናዎች የሚሰጡባቸውን ቀናት ይፋ አደረገ።

በዚህም መሰረት የሪሚዲያል ፕሮግራም ሀገር አቀፍ ፈተና ከግንቦት 17 እስከ 20፣ የቅደመ ምረቃ ትምህርት መውጫ ፈተና ከሰኔ 2 እስከ 12 እንዲሁም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሰኔ 24 እስከ ሐምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ይሰጣል፡፡

በተመሳሳይ የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና ከሐምሌ 29 እና 30 ቀን 2018 ዓ.ም ሲሰጥ፤ የመሰረታዊ የንብባና የስሌት ክህሎት ምዘና ፈተና ከሚያዚያ 26 እስከ ግንቦት 7 ቀን 2018 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት ውስጥ ይሰጣል፡፡

የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር )÷ እስከ ተጠቀሱት ጊዜያት ድረስ ተፈታኞች አስፈላጊውን የይዘትና የስነ-ልቦና ዝግጅት እንዲደርጉ አስገንዝበዋል።

ወላጆች፣ መምህራንና በየደረጃው ያለው የትምህርት አመራር ተፈታኞቻቸው የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ተገቢውን ድጋፍና ክትትል  ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል፡፡

በመሳፍንት እያዩ

Exit mobile version