አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በእንግሊዝ ኤፍ ኤ ዋንጫ ማንቼስተር ሲቲ ሳውዝሃምፕንን 2 ለ 1 በማሸነፍ ለፍጻሜ ደርሷል።
ምሽት 1 ሰዓት ከ20 ጀምሮ በተደረገው ጨዋታ ሳውዝሃምፕተን ፊን አዛዝ ባስቆተራት ግብ መምራት ቢችልም፤ ጀርሚ ዶኩ እና ኒኮ ጎንዛሌዝ ባስቆጠሯቸው ግቦች ማንቼስተር ሲቲ ለፍጻሜ ያበቃውን ድል አስመዝግቧል።
ውጤቱን ተከትሎም ማንቼስተር ሲቲ በኤፍ ኤ ዋንጫ ፍጻሜ ከሊድስ እና ቼልሲ አሸናፊ ጋር የሚጫወት ይሆናል፡፡
ማንቼስተር ሲቲ በተከታታይ 4ኛ ጊዜ ለኤፍ ኤ ዋንጫ ፍጻሜ በመድረስ አዲስ ክብረወሰን አስመዝግቧል።

