Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከ6 ቢሊየን ብር በላይ ወጪ 1 ሺህ 452 ትምህርት ቤቶች ሊገነቡ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 20፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ከ6 ቢሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ 1 ሺህ 452 የቅድመ አንደኛ ትምህርት ቤቶች ሊገነቡ ነው አለ የትምህርት ሚኒስቴር፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ትምህርት ቤቶቹን ሚኒስቴሩ ከክልሎች ጋር በመተባባር በሁሉም ክልሎች አንደሚገነባ ተናግረዋል።

ትምህርት ቤቶቹ በአጭር ጊዜ ውስጥ በጥራት ተገንብተው ለ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ዝግጁ እንደሚሆኑ ገልጸዋል።

በዚህም 87 ሺህ 120 ህጻናት ወደ ትምህርት ቤት እንዲገቡ ያደርጋል ያሉት ሚኒስትሩ÷ የትምህርት ቤቶቹ ግንባታ ጥራት ያለውን ትምህርት ለማዳረስ የተያዘውን ግብ ለማሳካት የሚያግዝ መሆኑንም አመልክተዋል።

ለዚህም ሚኒስቴሩ ከሁሉም ክልል ትምህርት ቢሮዎች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር የስምምነት ሰነድ ተፈራርሟል።

በፌቨን ቢሻው

Exit mobile version