Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በቢሾፍቱ ከተማ እየመከረ ነው

አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 21 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በቢሾፍቱ ከተማ እየመከረ ነው።
 
የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ለሁለት ቀን በሚቆየው ስብሰባው ላይ የ2012 እቅድ አፈፃፀምን ከመገምገሙም ባለፈ የ2013 መነሻ እቅድ ላይም ይመክራል ተብሏል።
 
የሊጉ አባላት መዋጮ አሰባሰብ ረቂቅ መመሪያም ምክክር ተደርጎበት ይፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል።
 
ከዚያም ባለፈ የሊጉን ሁለንተናዊ ስራ የሚደግፍ አማካሪ ምክር ቤት የማቋቋም ሃሳብም ይመከርበታል ነው የተባለው ።
 
የሴቶች ሊጉ አመራሮች በስብሰባው ማጠናቀቅያ ላይ ሊጉ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ያሰባሰበውን የምግብ፣ አልባሳትና ሌሎች ቁሳቁሶች በሻሸመኔና አርሲ ነጌሌ ከተሞች ጉዳት ለደረሰባቸው ሴቶች ድጋፍ እንደሚያደርግ ከብልጽግና ፓርቲ የፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
 
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።
Exit mobile version