Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሀድያ ሆሳዕና እና መቐለ 70 እንደርታ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ29ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ሀድያ ሆሳዕና እና መቐለ 70 እንደርታ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

ቀን 7 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ የመቐለ 70 እንደርታን ግብ ኬኔዲ ገብረፃዲቅ ሲያስቆጥር የሀድያ ሆሳዕናን የአቻነት ግብ ደግሞ ፀጋዓብ ግዛው ከመረብ አሳርፏል።

የሊጉ መርሐ ግብር ሲቀጥል አርባ ምንጭ ከተማ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቀን 10 ሰዓት ላይ ይገናኛሉ፡፡

ነገሌ አርሲ ከፋሲል ከነማ ቀን 9 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም ጨዋታቸውን የጀመሩ ሲሆን÷ኢትዮጵያ ቡና ከወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ደግሞ ምሽት 12 ሰዓት ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

Exit mobile version