Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ነገሌ አርሲና ፋሲል ከነማ አቻ ተለያዩ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ29ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ነገሌ አርሲ እና ፋሲል ከነማ ያለምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል፡፡

ቀን 9 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ሁለቱም ቡድኖች ግብ ሳያስቆጥሩ ወጥተዋል፡፡

በዚሁ ስታዲየም ኢትዮጵያ ቡና ከወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ምሽት 12 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

አስቀድሞ ቀን 7 ሰዓት ላይ በአዲስ አበባ ስታዲየም በተደረገ በሌላ የሊጉ ጨዋታ
መቐለ 70 እንደርታ እና ሀድያ ሆሳዕና 1 አቻ መለያታቸው ይታወቃል፡፡

በተመሳሳይ ስታዲየም ቀን 10 ላይ መደረግ የጀመረው የአርባ ምንጭ ከተማ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጨዋታ ያለ ምንም ግብ ቀጥሏል፡፡

Exit mobile version