አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 22፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ29ኛ ሳምንት የሲቢኢ ኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ኢትዮጵያ ቡናን 4 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
ምሽት 12 ሰዓት ላይ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም በተደረገ ጨዋታ ለወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ኮንኮኒ ሀፊዝ (ሁለት)፣ ያሬድ ከበደ እና በየነ ባንጃ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
የኢትዮጵያ ቡናን ግቦች አቡበከር አዳሙ እና በረከት ብርሃኑ ከመረብ አገናኝተዋል።
አስቀድሞ በተደረጉ የዕለቱ መርሐ ግብር አርባ ምንጭ ከተማ እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንዲሁም ነገሌ አርሲ እና ፋሲል ከነማ 0 ለ 0፤ መቐለ 70 እንደርታ እና ሀድያ ሆሳዕና 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት ተለያይተዋል።

