Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ዓለም አቀፍ የቡና ምርምር ጉባኤ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 24፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ዓለም አቀፍ የቡና ምርምር ጉባኤ “ከማሳ እስከ ዓለም አቀፍ ገበያ” በሚል መሪ ሐሳብ በቦንጋ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ይገኛል።

የቡና ዘርፉን የሚያሻሽሉ ጠንካራ እና ዘላቂ አሠራሮችን ለመተግበር ያስችላል በተባው ጉባኤ የተለያዩ የምርምር ስራዎች ቀርበዋል።

የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ደገላ ኤርገኖ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ጉባዔው ዓለም አቀፍ ትሥሥር የሚፈጥርና ምርትን የሚያሳድግ ሐሳብ የተነሳበት ነው።

በትምህርት ሚኒስቴር የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ሥራ አስፈጻሚ ሠራዊት ሀንዲሶ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ የኢትዮጵያን የቡና ገበያ ለማሻሻል ጥናቶች ወደ ተግባር መግባት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

ዓለም አቀፍ የቡና ምርምር ጉባኤው በነገው ዕለት ይጠናቀቃል።

በዐምደወርቅ ሽባባው

Exit mobile version