Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ማንቼስተር ዩናይትድ ከሊቨርፑል …

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 25፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ35ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ማንቼስተር ዩናይትድ በሜዳው ኦልድ ትራፎርድ ሊቨርፑልን የሚያስተናግድበት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡

ቀን 11 ሰዓት ከ30 ላይ በሚደረገው ጨዋታ በማንቼስተር ዩናይትድ በኩል ማቲያስ ዲላይት በጉዳት፤ ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ ደግሞ በቅጣት ምክንያት አይሰለፉም፡፡

በጉዳት እየታመሰ በሚገኘው ሊቨርፑል ስብስስብ ውስጥ ደግሞ ሞሀመድ ሳላህ፣ አሊሰን ቤከር፣ ኮኖር ብራድሌይ፣ ዋታሮ ኢንዶ እና ሁጎ ኤኪቲኬ ለጨዋታው እንደማይደርሱ ተረጋግጧል፡፡

ማንቼስተር ዩናይትድ 61 ነጥቦችን በመሰብሰብ በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ 3ኛ ላይ የሚገኝ ሲሆን፤ ሊቨርፑል ደግሞ በ58 ነጥብ 4ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡

በጨዋታው ማንቼስተር ዩናይትድ ደረጃውን ለማስጠበቅ እንዲሁም ሊቨርፑል ደረጃውን በማሻሻል የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ተሳትፎውን ለማረጋገጥ የሚፋለሙ ይሆናል፡፡

በሌሎች የሳምንቱ መርሐ ግብር ጨዋታዎች ቦርንማውዝ ከክሪስታል ፓላስ ቀን 10 ሰዓት እንዲሁም አስቶን ቪላ ከቶተንሃም ሆትስፐር ምሽት 3 ሰዓት ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

Exit mobile version