Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በሰሜን ሸዋ ዞን ከፍተኛ ንፋስ በቀላቀለ ዝናብ ከ11 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ

አዲስ አበባ፤ ነሀሴ 21 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን አንኮበር ወረዳ ከፍተኛ ንፋስ በቀላቀለ ዝናብ ከ 11 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።

የአንኮበር ወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት የአደጋ መከላከልና ፈጣን ምላሽ ቡድን መሪ አቶ ሰለሞን ሽፈራ÷ አደጋው የተከሰተው ለነሃሴ 20 አጥቢያ መሆኑን ገልጸዋል ።

ተፈጥሯዊ አደጋው ያስከተለው ጉዳትም ከ 11 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት መሆኑን አቶ ሰለሞን ገልፀዋል።

በአደጋው ሳቢያ በአልዩ አምባ ከተማ እናበ ዙሪያዋ በሚገኙ ቀበሌዎች 355 መኖሪያ ቤቶች ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ተገልጿል።

ከዚያም ባለፈም በአደጋው በመንግስት መስሪያ ቤቶች፣ትምህርት ቤቶች እና የእምነት ተቋማት ላይ ጉዳት የደረሰ ሲሆን በሰው ህይወት ላይ ጉዳት አለመድረሱም ነው የተገለጸው ።

በሰላም አሰፋ

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

Exit mobile version