Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከጳጉሜ እስከ ጳጉሜ እንደርሳለን” በሚል መሪ ሃሳብ በመጪው ዓመት የመንገድ ደህንነት ንቅናቄ ይካሄዳል – የትራንስፖርት ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 21፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)”ከጳጉሜ እስከ ጳጉሜ እንደርሳለን” በሚል መሪ ሃሳብ በመጪው 2013 ዓ.ም የመንገድ ደህንነት ንቅናቄ እንደሚካሄድ የትራንስፖርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ንቅናቄውን አስመልክቶ የትራንስፖርት ሚንስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ መግለጫ ሰጥተዋል።

ንቅናቄው ዓመቱን ሙሉ የሚካሄድ መሆኑ የገለፁት ሚኒስትሯ የመንገድ ደህንነትን በማስጠበቅ የዜጎችን ህይወት ከአደጋ መታደግ ይገባል ብለዋል።

ንቅናቄው ከጳጉሜ 1 ጀምሮ በተለያዩ መርሃ ግብሮች እንደሚጀምር የተናገሩት ወይዘሮ ዳግማዊት በንቅናቄው የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብሮች፣ የቁጥጥር እና ማስተማሪያ ተግባራት እና የተለያዩ ውይይቶች ይካሄዳሉ፡፡

በዚህም የሲቪክ ማህበራት፣ የመገናኛ ብዙሃን እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ይሳተፉበታል ነው የተባለው።

በተጨማሪም ሚንስቴሩ በተለይ በትራፊክ አደጋ ህይወታቸው የሚያልፉ ዜጎችን ቁጥር በከፍተኛ መጠን ለመቀነስ በትኩረት እየተሰራ ነው ያለ ሲሆን በዚህም በ2010 ዓ.ም በ10 ሺህ ተሽከርካሪ ይደርስ የነበረውን 54 የሞት ምጣኔ ፤በ2012 በ10 ሺህ ተሽከርካሪ ወደ 34 የሞት ምጣኔ ማውረድ ተችሏል።

የትራንስፖርት ሚንስቴር በ2012 ዓ.ም “እንደርሳለን” በሚል መሪ ሃሳብ የመንገድ ደህንነት ንቅናቄ መካሄዱ ይታወሳል።

በምስክር ስናፍቅ

#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

Exit mobile version