Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ መታሰቢያ ሐውልት ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 27፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ አፍሪካ ፓርክ የተገነባው የአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ መታሰቢያ ሐውልት ተመርቋል።

የመታሰቢያ ሐውልቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በይፋ መርቀዋል።

በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም አርቲስቶች ተገኝተዋል።

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ የሀገር ባለውለታ ለሆኑና በጥበብ ሙያቸው ለኢትዮጵያ ሀገራችን ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽዖ በከተማችን አዲስ አበባ የመታሰቢያ ሐውልት ቆሞላቸዋል ብለዋል።

በመልዕክታቸውም ጥበብ ሀገር ትሠራለች፤ ሀገርም ጠቢብን ታከብራለች ነው ያሉት።

በዙፋን ካሳሁን

Exit mobile version