Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አፍሪካውያን የማህበራዊ ሚዲያ ይዘት ፈጣሪዎች በአዲስ አበባ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 28፣ 2018 (ኤፍኤምሲ) አፍሪካውያን የማህበራዊ ሚዲያ ይዘት ፈጣሪዎች የአህጉሪቷን ትክክለኛ ገጽታ ለዓለም በማስተዋወቅ ረገድ እንደ አምባሳደር እያገለገሉ ይገኛሉ።
የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ በፐልስ ኦፍ አፍሪካ (Pulse of Africa-POA) ከኤ.ጂ.ኤ የቴክኖሎጂ ኢንተርፕራይዝ (AGA-Tech) ትብብር በአዲስ አበባ ዓድዋ ድል መታሰቢያ ነገ እና ከነገ በስቲያ ይካሄዳል።
“ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ለተሻለች አፍሪካ” በሚል መሪ ሃሳብ በሚካሄደው ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ የአህጉሪቱ የማህበራዊ ሚዲያ ይዘት ፈጣሪዎች አዲስ አበባ ገብተዋል።
የአህጉሪቷ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች፣ ፖሊሲ አውጪዎች፣ ዳያስፖራዎችና የግሉ ዘርፍ ተዋናዮች የረጅም ጊዜ ትብብር የሚፈጥሩበት ይህ መድረክ የኢትዮጵያን ብሎም የአፍሪካን ትክክለኛ ትርክት ለዓለም ለማስተዋወቅ ወሳኝ ነው።
ታዋቂው የአፍሪካዊ ዲጂታል ታሪክ ተራኪ ጋናዊው በርትሆልድ ኮቢ ዊንክለር አክኮን (ዎዴ ማያ) ጨምሮ የአህጉሪቷ ማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች አዲስ አበባ መግባት ጀምረዋል።
ጋናዊው በርትሆልድ ኮቢ ዊንክለር አክኮን (ዎዴ ማያ) እንዳለው፤ የአፍሪካን የይዘት ፈጠራ ባለሙያዎች በአንድ መድረክ በተለይም በአዲስ አበባ ማግኘት እጅግ የሚያስደስት ነው፡፡
የይዘት ፈጣሪዎቹ በአንድ አዳራሽ ተገኝተው የአፍሪካን አጀንዳ ለቀሪው ዓለም ለማድረስ የሚያደርጉት ምክክር ትልቅ ፋይዳ እንዳለው መግለጹን ፐልስ ኦፍ አፍሪካ ዘግቧል።
Exit mobile version