Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ከ9 ሺህ ኪ.ሜ በላይ አዲስ የዲስትሪቢዩሽን መስመሮች ማስፋፊያ ስራ ተከናወነ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ባለፉት ዘጠኝ ወራት 9 ሺህ 588 ኪሎ ሜትር አዳዲስ የዲስትሪቢዩሽን መስመሮች ማስፋፊያ ተከናውናል አለ የኢትየጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት።

በዲስትሪቢዩሽን መስመሮች ማስፋፊያው የኃይል መቆራረጥ ድግግሞሽና የቆይታ ጊዜን መቀነስ መቻሉን የገለጸው አገልግሎቱ÷ 3 ሺህ 518 ኪሎ ሜትር የመካከለኛ መስመር እንዲሁም 6 ሺህ 69 ኪሎ ሜትር የዝቅተኛ መስመር ዝርጋታ መከናወኑን ገልጿል።

በተጨማሪም የኃይል አቅርቦቱን የሚያሳድጉ 3 ሺህ 683 የተለያዩ ዓቅም ያላቸው አዲስ የዲስትሪቡዩሽን ትራንስፎርመሮች መተከላቸውን አመልክቷል።

ነባሩ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት አቅም ከማሻሻልና የኃይል መቆራረጥን ከመቀነስ አኳያም 62 ሺህ 274 ኪሎ ሜትር የሚሸፍን የመካከለኛ መስመር እና በ67 ሺህ 131 ትራንስፎርመሮች ላይ የቅድመ መከላከል ምርመራ ተካሂዷል፡፡

በዲስትሪቢዩሽን ኔትወርክ ላይ ከተገኙት ለኃይል መቆራረጥ መንስኤ ከሆኑ 92 ከመቶ ግኝቶች እንዲሁም በዲስትሪቢዩሽን ትራንስፎርመሮች 86 ከመቶ የማስተካከያ ርምጃዎች ተወስዶባቸዋልም ነው ያለው አገልግሎቱ፡፡

ባለፉት ዘጠኝ ወራትም 3 ሺህ 99 ኪሎ ሜትር የመካከለኛና ዝቅተኛ መስመር መልሶ ግንባታ መከናወኑንና በ1 ሺህ 579 ነባር የዲስትሪቢዩሽን ትራንስፎርመሮች ላይ የአቅም ማሻሻያ መሰራቱን አገልግሎቱ ለፋና ዲጂታል የላከው መረጃ ያመላክታል።

Exit mobile version