አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የመጀመሪያው ሀገር አቀፍ የአርሶ አደሮች የምርምር ኮንፈረንስ በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው።
ኮንፈረንሱ አርሶ አደሮች በግብርና ህይወት ያሳለፏቸውን ተሞክሮ የሚያጋሩበት፣ ሀገር በቀል ልምዳቸውን የሚያቀርቡበት፣ ችግሮቻቸውን የሚወያዩበት እና ከዩኒቨርሲቲው የምርምር ዘርፍ ሐሳብ የሚሰጥበት መሆኑ ተገልጿል።
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ብርሃነመስቀል ጠና (ዶ/ር) በዚህ ወቅት÷ አርሶ አደሮች በትጋትና በጥራት የኢትዮጵያ ብልፅግናን የሚያረጋግጡ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ኮንፈረንሱ መሬት ላይ ያለ እውቀት የሚፀናበትና ከገበሬው ለገበሬ ሐሳብ የሚቀርብበት መሆኑንም አመልክተዋል።
አርሶ አደሮች በቂ የሆነ የቴክኖሎጂ አቅርቦት በሌለበት ከእንስሳት እስከ ሰብል ልማት ስራ ውጤት ለማስመዝገብ የበኩላቸውን አስተዋጽዖ እያበረከቱ መሆናቸውም በመድረኩ ተነስቷል::
በአዳነች አበበ

