Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የለውጡ መንግሥት ጥልቅ የሆኑ የሚዲያ ሪፎርሞችን አድርጓል – ወ/ሮ ሀይማኖት ዘለቀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ‌‌‎የለውጡ መንግሥት ጥልቅ የሆኑ የሚዲያ ሪፎርሞችን አድርጓል አሉ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሀይማኖት ዘለቀ።

‎ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት “የሚዲያ እመርታ ለትርክት ግንባታ” በሚል መሪ ሐሳብ ሀገራዊ የምክክር መድረክ መካሄድ ጀምሯል።

ዋና ዳይሬክተሯ በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ከለውጡ በፊት የሚዲያ ተቋማት ዘርፈ ብዙ ስብራቶች ነበሩባቸው፤ ከእነዚህም ጥቂቶቹ የፖሊሲ እና የማዕቀፍ፣ የመዋቅር አደረጃጀት፣ ተቋማዊና የትክክለኛ ሙያዊ ስነ ምግባር ስብራቶች ይገኙበታል።

‎የለውጡ መንግሥት እነዚህን ስብራቶች ለማከም ጥልቅ የሆኑ የሚዲያ ሪፎርሞችን አድርጓል ብለዋል።

ሪፎርሙ ካሳካቸው ለውጦች መካከል ተጠሪነቱ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሆነ የመገናኛ ብዙኃን ባልስልጣን ማቋቋም፣ የመገናኛ ብዙኃን የእርስ በእርስ ቁጥጥር ስርዓት መፍጠር፣ እንዲሁም ዘርፉ እራሱን በራሱ እንዲቆጣጠር የሚያስችሉ የሙያ ማህበራትን ማበራከት ዋነኞቹ መሆናቸውን ገልጸዋል።

እነዚህ ሪፎርሞች ትክክለኛ ውሳኔዎች ስለመሆናቸው በሚከተሉት አሃዛዊ ስኬቶች ታጅቧልም ነው ያሉት።

👉የመገናኛ ብዙኃን ቁጥር ከለውጡ በፊት ከነበሩበት 122 ወደ 310 ከፍ ብሏል።

👉የሬድዮ ጣቢያዎች ከለውጡ በፊት ከነበሩበት 52 ወደ 126፤

👉የቴለቪዥን ጣቢያዎች ከለውጡ በፊት ከነበሩበት 25 ወደ 128፤

👉 የመገናኛ ብዙኃን የቋንቋ ተደራሽነት ከለውጡ በፊት ከነበሩበት 39 ወደ 60፤

👉 35 የውጭ ሚዲያዎችና 50 የማህበረሰብ ሚዲያዎች የኢትዮጵያ የሚዲያ ምህዳር አካታችነትን በመፍጠር ላስመዘገበው ስኬት አይነተኛ ማሳያዎች ናቸው ማለታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ አመላክቷል።

Exit mobile version