አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሚዲያው ዘርፍ የተደረጉ ማሻሻያዎች የሬዲዮ ጣቢያዎች ሀገርን በመገንባት ሂደት ውስጥ ወሳኝ ሚናቸውን እንዲጫወቱ አስችሏል አሉ የአዋሽ ኤፍ ኤም ዋና ስራ አስኪያጅ አብዱ መሀመድ (ዶ/ር)።
አብዱ (ዶ/ር) ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት እየተካሄደ በሚገኘው ”የሚዲያ እመርታ ለትርክት ግንባታ” በተሰኘ ሀገራዊ የምክክር መድረክ ላይ የለውጡ መንግሥት ለዘርፉ ያበረከታቸውን ትሩፋቶች አብራርተዋል።
የቁጥጥር እና የፖለቲካ ገደቦች፣ የአቅምና የሙያ ክፍተቶች፣ የፋይናንስና የቴክኖሎጂ ገደቦች ዘርፉንና ተቋሙን ሲፈትኑ የከረሙ ስር የሰደዱ ችግሮች እንደነበሩ አንስተዋል።
እነዚህ ችግሮች የፖሊሲ እና የህግ ማሻሻያዎችን በማድረግ፣ ለኢንቨስትመንት ትኩረት በመስጠት የሬዲዮ ጣቢያዎች ከመበራከታቸው ባለፈ የጋራ እሴቶችን በማጠናከርና ማህበረሰብን በማስተሳሰር እንዲሁም ሀገርን በመገንባት ሂደት ውስጥ ወሳኝ ሚናቸውን እንዲጫወቱ አስችሏል ማለታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ አመላክቷል።

