Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሃላባ ከተማ የከፍተኛ ሊጉ አጠቃላይ አሸናፊ ሆነ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ሃላባ ከተማ በመለያ ምት ጋሞ ጨንቻን 4 ለ 3 በማሸነፍ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ አጠቃላይ አሸናፊ ሆኗል።

የ2018 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የማጠቃለያ የፍፃሜ ጨዋታ ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም ተካሂዷል።

በፍፃሜው ሃላባ ከተማን ከጋሞ ጨንቻ ያገናኘው ጨዋታ በመደበኛ ክፍለ ጊዜ ያለ ግብ አቻ ተጠናቅቋል።

የዋንጫውን አሸናፊ ለመለየት በተደረገ የመለያ ምት ሃላባ ከተማ ጋሞ ጨንቻን 4 ለ 3 በማሸነፍ የከፍተኛ ሊጉ አጠቃላይ የዋንጫ አሸናፊ ሆኗል።

አስቀድሞ ለደረጃ በተደረገ ጨዋታ ደሴ ከተማ የካ ክፍለ ከተማን 1 ለ 0 በማሸነፍ 3ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቅቋል።

በእንዳልካቸው ወዳጄ

Exit mobile version