Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሥነ ምግራባዊ የሆነ ትግበራ የሚፈልገው ሰው ሰራሽ አስተውሎት …

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ሥነ ምግባራዊ በሆነ መንገድ መደገፍ እና መመራት አለበት።

የመጀመሪያው የአፍሪካ የማህበራዊ ሚዲያ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ (ASMIS-2026) በዓድዋ ድል መታሰቢያ “ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ለተሻለች አፍሪካ” በሚል መሪ ሃሳብ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ባለሙያዎች እና በአፍሪካ ከፍተኛ ተከታይ ያላቸው የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎችን በማሳተፍ ሰው ሰራሽ አስተውሎት ለይዘት ፈጠራ እድገት ያለውን ፋይዳ የሚዳስስ የፓናል ውይይት ተካሂዷል።

በፓናል ውይይቱ ቴክኖሎጂው ፈጠራ የታከለባቸው ይዘቶችን ከመቅረጽ ባለፈ ስራዎች የሚከናወኑበትን ፍጥነት በከፍተኛ ደረጃ እንደሚጨምር በዚሁ ወቅት ተመላክቷል።

ይሁን እንጂ ከቴክኖሎጂው ጋር ተያይዘው የሚመጡ ስጋቶችን ለመከላከል አጠቃቀሙን ሥነ ምግባራዊ በሆነ መንገድ መምራትና በፖሊሲ መደገፍ እንደሚገባ ተነስቷል።

አፍሪካ በዲጂታል ዘርፍ ያላትን አቅም ለማሳደግና ሰው ሰራሽ አስተውሎትን ለበጎ ተግባር ለማዋል አዲስ አቅጣጫ ጠቋሚ ነው መባሉንም የኢትዮጵያ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት መረጃ ያመላክታል።

Exit mobile version