Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በሩሲያ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት በ13 የአውሮፕላን ማረፊያዎች አገልግሎት ተቋረጠ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በደቡባዊ ሩሲያ ሮስቶቭ ኦን ዶን ከተማ በሚገኘው የበረራ አስተዳደር ህንፃ ላይ በተፈፀመ የድሮን ጥቃት በ13 የአውሮፕላን ማረፊያዎች አገልግሎት ተቋርጧል፡፡

በዛሬው ዕለት በተፈፀመው ጥቃት በሰራተኞች ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ የሀገሪቱ ትራንስፖርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በጥቃቱ ምክንያት በአውሮፕላን ማረፊያዎቹ የተቋረጠውን አገልግሎት ለመመለስ ጥረት እየተደረገ መሆኑም ተገልጿል፡፡

ጥቃቱ ሩሲያ በ2ኛው የዓለም ጦርነት በናዚ ጀርመን ላይ የተቀዳጀችውን ድል 81ኛ ዓመት እያከበረች ባለበት ወቅት መፈጸሙ ነው የተገለፀው፡፡

ሩሲያና ዩክሬን በነገው ዕለት የሚከበረውን የድል በዓል ምክንያት በማድረግ የሁለት ቀን የተናጥል የተኩስ አቁም አውጀው እንደነበር ይታወሳል፡፡

ይሁን እንጂ በሩሲያ የበረራ አስተዳደር ህንፃ የተፈጠረውን የድሮን ጥቃት ተከትሎ ሁለቱ ሀገራት በተኩስ አቁም ጥሰት እርስ በእርስ እየተወነጃጀሉ ይገኛሉ፡፡

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ሩሲያ ተኩስ አቁሙን በመጣስ 840 የድሮን ጥቃት ፈጽማለች ሲሉ፥ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ኬቭ የተኩስ አቁሙን በመጣስ ከ1 ሺህ 300 በላይ ጥቃቶችን ሰንዝራለች ሲል ከሷል፡፡

 

በሚኪያስ አየለ

Exit mobile version