አዲስ አበባ፤ ነሀሴ 21 ፣2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ)ለአዲስ አበባ የሰላም ምክር ቤት ፕሬዚዳንት እና ምክትል ፕሬዚዳንት መመረጡን ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አስታወቁ።
ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ ÷ዛሬ ለተቋቋመው የአዲስ አበባ የሰላም ምክር ቤት የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና ፕሬዚዳንት፣ አርቲስት መቅደስ ፀጋዬ ደግሞ ምክትል ፕሬዚዳንት ሆነው መመረጣቸውን ገልጸዋል።
ወይዘሮ አዳነች አያይዘውም “ተመራጮች ለአዲስ አበባችን የሠላም ጉዳይ ይመለከተናል በማለት ከነዋሪው ጋር በመሰለፋችሁ ያለኝን ታላቅ ክብር እና አድናቆት እየገለፅኩ ከፊታችሁ ትልቅ ሥራ የሚጠበቅባችሁ መሆኑን ሳልገልፅ አላልፍም።” ብለዋል።
በመሆኑም ለከተማዋ ሁለንተናዊ ብልፅግና የዕለት ተዕለት ሰላም ወሳኝ በመሆኑ ይህ የሰላም ምክር ቤት የተጣለበትን ሕዝባዊ አደራ እና ይዞት የተነሳዉን በጎ ዓላማ ከግብ በማድረስ ታሪካዊ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ ከአደራ ጭምር አሳስባለሁ ብለዋል።
ከዚያም ባለፈ ሁሉም ዜጋም ለሰላም ዘብ እንዲቆም ምክትል ከንቲባዋ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
#FBC
የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

