Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

የአፍሪካ ሀገራት ከኢትዮጵያ ኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ተሞክሮ ሊወስዱ ይገባል – ኤሊቪስ ሚሺላ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 30፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የመጀመሪያው የማህበራዊ ሚዲያ ተጽእኖ ፈጣሪዎች ጉባኤ (ASMIS2026) በአዲስ አበባ ዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተካሄደ ይገኛል።
በመድረኩ ለመሳተፍ አዲስ አበባ የሚገኘው ኬኒያዊው የማህበራዊ ሚዲያ ተጽእኖ ፈጣሪ ኤሊቪስ ሚሺላ እንዳለው÷ በኢትዮጵያ እየተሰራ ያለው እና አዲስ አበባን ውብ ያደረገው የኮሪደር ልማት ስራ እጅግ ያስደንቃል።
ስራው አዲስ አበባን ውብ፣ ማራኪና ተወዳጅ ከተማ አድርጓታል ብሏል።
የአፍሪካ መዲና የሆነችው አዲስ አበባ በጣም ውብ እና ጽዱ ሆናለች በማለት ገልጾ÷ የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቱን ተሞክሮ ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ሊወስዱት ይገባል ነው ያለው።
እኛ አፍሪካዊያን እርስ በርስ የምናጋራው ነገር አለን፤ ሁሉንም ነገር ከሌሎች አህጉራት ማስገባት አይጠብቅብንም እርስ በርስ ተሞክሮ ልንለዋወጥ ይገባል ሲልም ቁጭቱን ገልጿል፡፡
እንደ አህጉር ለአፍሪካ ልህቀት እጅና ጓንት ሆነን በቅንጅት ልንሰራ ይገባል በማለት መልዕክት አስተላልፏል፡፡
በአመለወርቅ ደምሰው
Exit mobile version