Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ፕሬዚዳንት ትራምፕ በቻይና የስራ ጉብኝት ያደርጋሉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዚህ ሳምንት ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ወደ ቻይና እንደሚያቀኑ ተነግሯል፡፡
ከአስር ዓመታት በኋላ በስልጣን ላይ ያለ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ቻይናን ሲጎበኝ ይህ የመጀመሪያው መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ ፕሬዚዳንት ትራምፕ በቻይና ጉብኝት የሚያደርጉ መሆኑን ቤጂንግ አረጋግጣለች፡፡
ፕሬዚዳንት ትራምፕ በቆይታቸው ከቻይና አቻቸው ሺ ጂንፒንግ ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል፡፡
በጉብኝቱ የቦይንግ፣ ሲቲግሩፕ እና ኳልኮም ኩባንያ የበላይ ሀላፊዎች ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ወደ ቻይና እንደሚጓዙ ተጠቁሟል።
የፕሬዚዳንቱ ጉብኝት በዋሽንግተን እና ቤጂንግ መካከል ያለውን የታሪፍ መካረር ለማለዘብ እንደሚረዳ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ፕሬዚዳት ትራምፕ በመጪው ረቡዕ ወደ ቤጂንግ ያቀናሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በአቤል ነዋይ
Exit mobile version