አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘገየ አስፋው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።
ኮሚሽነር ዘገየ አስፋው በግብርና ሚኒስቴር ከ1968–1970 ዓ.ም እና ከ1983 – 1984 ዓ.ም በሚኒስትርነት አገልግለዋል።
እንዲሁም የመሬት ለአራሹ አዋጅ እንዲታወጅ ከፍተኛ ድርሻም አበርክተዋል።
ኮሚሽነር ዘገየ አስፋው ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው በዛሬው ዕለት ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል፡፡

