አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ለሀገር ልማትና ዕድገት ይበጃል ለሚሉት የፖለቲካ ፓርቲ ድምፅ ለመስጠት ተዘጋጅተናል አሉ።
በአዲስ አበባ ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በመመዝገብ ካርድ የወሰዱ ነዋሪዎች ለ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ካርድ ከማውጣት ጀምሮ የምርጫውን ቀን በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
እንዲሁም በምርጫ ካርዳቸው ለሀገር ልማትና ዕድገት ዕውን መሆን ለሚሰራ ፓርቲ ይሁንታ ለመስጠት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።
ምርጫ ለጠንካራ ሀገረ መንግሥት ግንባታ ወሳኝ መሆኑን በመጠቆም÷ በ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ድምፅ መስጠት የሚያስችላቸውን ዝግጅት ማድረጋቸውን የኢዜአ መረጃ ያመላክታል።
የምርጫ ካርድ በማውጣት ለሀገር ይበጃል የሚሉትን ፓርቲ ለመምረጥ የድምፅ መስጫ ቀኑን እየተጠባበቁ እንደሚገኙም አረጋግጠዋል።
በአጠቃላይ ምርጫው ሕገ መንግሥታዊ የመምረጥና መመረጥ ዴሞክራሲያዊ ማረጋገጫ ወሳኝ መድረክ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል።
ዜጎች በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ግንቦት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ለሀገር ልማትና ዕድገት ይበጃል ለሚሉት ፓርቲ ድምፅ ይሰጣሉ።

