Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ብሪክስ ለሰላም፣ ለጋራ ደኅንነትና ለልማት መጠናከር ግንባር ቀደም ሚና መጫወት አለበት – ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ብሪክስ ለሰላም፣ ለጋራ ደኅንነት እና ለልማት መጠናከር ግንባር ቀደም ሚና መጫወት አለበት አሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር)።
የብሪክስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጉባኤ “ለጥንካሬ፣ ለፈጠራ፣ ለትብብር እና ለዘላቂነት መገንባት” በሚል መሪ ሐሳብ በሕንድ ኒው ዴልሂ እየተካሄደ ይገኛል።
በጉባኤው የተሳተፉት ጌዲዮን ጢሞቴዎስ (ዶ/ር) እንዳሉት÷ ሁሉንም ሀገራት በፍትሃዊነት የሚያገለግል ዓለም አቀፍ ስርዓትን ለመገንባት የተቀናጀ የባለብዙ ወገን ጥረት በአስቸኳይ ያስፈልጋል።
አሁን ያለው የዓለም አቀፍ ቀውስ በአስቸኳይ ካልተፈታ በሀገራት ድንበር የማይገታ አስከፊ የኢኮኖሚ፣ የፋይናንስ እና የማኅበራዊ አለመረጋጋት እንደሚያስከትልም አስገንዝበዋል።
በዚህም ብሪክስ ለሰላም፣ ለጋራ ደኅንነት እና ለልማት መጠናከር ግንባር ቀደም ሚና በመጫወት ፍትሃዊ እና የተረጋጋ ዓለም አቀፍ ስርዓትን ለመገንባት የበኩሉን ሚና መጫወት እንዳለበት አጽንኦት መስጠታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።
Exit mobile version