አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአትሌት የብርጓል መለሰ ሥርዓተ ቀብር በዛው ዕለት ተፈጽሟል።
የአትሌቷ ሥርዓተ ቀብር በመንበረ ፀባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴደራል ቤተሰቦቿ፣ ወዳጅ ዘመዶቿ፣ የመከላከያ ሠራዊት አመራር እና አባላት በተገኙበት በመከላከያ የክብር ዘብ እና ማርሽ ባንድ በመታጀብ ነው የተፈጸመው።
የረጅም ርቀት ሯጭ አትሌት የብርጓል መለሰ ኢትዮጵያን በዓለም አቀፍ የጎዳና ላይ ውድድሮች ስታስጠራ ቆይታለች፡፡
አትሌቷ ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ጀምሮ በበርካታ አሕጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ውድድሮች ላይ በመካፈል ስኬታማ ጊዜያትን በአትሌቲክሱ ማሳለፏም የሚታወስ ነው፡፡
ሚያዚያ 1982 ዓ.ም የተወለደችው አትሌት የብርጓል ግንቦት 4 ቀን 2018 ዓ.ም ማለዳ በጃን ሜዳ የስፖርት ማዘውተሪያ ባገጠማት ድንገተኛ አደጋ በ36 ዓመቷ ከዚህ ዓለም በሞት ተለይታለች።

