Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ፕሬዚዳንት ትራምፕ የአይኤስ መሪ መገደሉን አስታወቁ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዓለም አቀፍ ደረጃ የአይኤስ አይኤስ ሁለተኛ መሪ መሆኑ የሚነገረውን አቡ ቢላል አል ሚኑኪ መገደሉን አስታወቁ፡፡
ፕሬዚዳንት ትራምፕ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳስታወቁት፤ አቡ ቢላል አል ሚኑኪ የተገደለው የአሜሪካ እና ናይጄሪያ የጦር ሃይሎች በጥምር ባካሄዱት ኦፕሬሽን ነው፡፡
ዋሽንግተን አቡ ቢላል አል ሚኑኪን በፈረንጆቹ 2023 ዓለም አቀፍ አሸባሪ በማለት መፈረጇ የሚታወስ ሲሆን፤ አሸባሪ ቡድኑ ውስጥ ከፍተኛ ተሰሚነት ያለው ሁለተኛው መሪ መሆኑ ይነገራል።
የናይጄሪያ ጦር በጉዳዩ ላይ እስካሁን ያለው ነገር የለም።
አል ሚኑኪ የቡድኑን የአፍሪካ ሴል የሚመራ ሲሆን በተለይም በቻድ፣ ኒጀር እና ማሊ በስፋት የሚቀሳቀሰውን ቡድን በበላይነት ይመራ እንደነበር ተሰምቷል፡፡
ፕሬዚዳንት ትራምፕ የአል ሚኑኪ ግድያ አሸባሪ ቡድኑን በአፍሪካ ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ ክፉኛ የሚጎዳው መሆኑን በመግለጽ የናይጄሪያ መንግስትን ለአጋርነቱ አመስግነዋል፡፡
በአቤል ነዋይ
Exit mobile version