አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በ24ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በ20 ኪሎ ሜትር የርምጃ ውድድር በሁለቱም ጾታ በቀዳሚነት በማጠናቀቅ የወርቅ ሜዳሊያዎችን አግኝታለች።
በሴቶች አትሌት ውብዓለም ሽጉጤ ውድድሩን በቀዳሚነት ስታጠናቅቅ፤ አትሌት ሕይወት አምባው 4ኛ እንዲሁም አትሌት ማሬ ቢተው 8ኛ ደረጃን በመያዝ ውድድራቸውን አጠናቅቀዋል፡፡
በወንዶች አትሌት ምስጋናው ዋቁማ ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ ማስገኘት የቻለ ሲሆን፤ አብዱልሰላም አብዱልዋሂብ 3ኛ ደረጃን በመያዝ የነሐስ ሜዳሊያ ለሀገሩ አምጥቷል።
በወርቅነህ ጋሻሁን

