Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ወጣት የኢንዱስትሪ አልሚዎች የሚገኙበት የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ…

‎አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ (ዶ/ር) የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክን የመጀመሪያ ምዕራፍ በዛሬው እለት መርቀው ከፍተዋል፡፡
በኢንዱስትሪ ፓርኩ ለግብርና ስራ የሚውል ፓምፕ፣ የወርቅ ማምረቻ፣ የመኖ ማቀነባበሪያ እና የብሎኬት ማምረቻ ፋብሪካ ማሽኖች ይመረታሉ።
ዛሬ ተመርቆ በተከፈተው የገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከሚገኙ ወጣት አልሚዎች መካከል የአሸናፊና ይርጋለም ብረታ ብረት ኢንጂነሪግ ዋና ስራ አስኪያጅ አሸናፊ ኃይለጊዮርጊስ አንዱ ነው፡፡
ድርጅቱ የእንጨት መሰንጠቂያ፣ የማርቭል መቁረጫ እንዲሁም የወርቅ ማጠቢያ ማሽኖችን እያመረተ እንደሚገኝ ገልጾ፥ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ምርቶቻቸውን ለገበያ ማቅረብ መጀመራቸውን አስረድቷል።
በተጨማሪም በአሁኑ ወቅት ከ50 እስከ 60 ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል መፍጠሩን ነው የገለጹት።
የዶሪ ኢንጂነሪንግ መስራችና ስራ አስኪያጅ ወጣት ምስጋናው በበኩሉ፥ መንግስት መስሪያ ቦታ መስጠትን ጨምሮ የተለያዩ ድጋፍ እያደረገላቸው እንደሚገኝ ተናግሯል።
ድርጅቱ የመኪና መለዋወጫዎችንና ለኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ የሚሆኑ ምርቶችን የሚያመርት ሲሆን፥ ከ50 በላይ ቋሚ ሰራተኞችና ከ100 በላይ ጊዜያዊ ሰራተኞች የሥራ እድል ተፈጥሮላቸዋል፡፡
በኢንዱስትሪ ፓርኩ ውስጥ የሚገኘው ጦሳ ኢንጂነሪግ የህክምና መገልገያዎች ማምረቻ ፋብሪካ በህክምናው ዘርፍ በመሰማራት የተለያዩ የህክምና መገልገያዎችን እያመረተ ይገኛል።
በሶስና አለማየሁ
Exit mobile version