Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ባለወርቅ ሜዳሊያው ሐኪም…

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ህክምና ትምህርት ክፍል በዛሬው ዕለት ካስመረቃቸው የ2018 ተመራቂ ተማሪዎች መካከል ዶ/ር ሙሉጌታ ደምስ አንዱ ነው።
ገና በልጅነቱ ሐኪም የመሆን ህልም እንደነበረው የተናገረው ዶ/ር ሙሉጌታ በዛሬው የምረቃ በዓል ላይ 3 ነጥብ 92 ውጤት በማስመዝገብ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆኗል።
ይህ ሽልማት የተለየ ስሜት እንደፈጠረለት የገለጸው ዶ/ር ሙሉጌታ፥ ዛሬ እኔ ሳልሆን ወላጆቼ ናቸው ያሸነፉት ብሏል።
ለዚህ ስኬቱ የበቃው በግል ጥረቱ፣ በጊዜ አጠቃቀሙ፣ በመምህራኑ ድጋፍና የወላጆቹ መስዋዕትነት መሆኑን ተናግሯል።
በሰለጠነበት የሕክምና ሙያ ሕዝቡን በታማኝነት ለማገልገል ዝግጁ መሆኑንም ነው የገለጸው።
በምናለ አየነው
Exit mobile version