Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

በዓለም የኤምኤምኤ ከባድ ሚዛን ውድድር ካሜሩናዊው ፍራንሲስ ንጋኑ በዝረራ አሸነፈ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በአሜሪካ ካሊፎርኒያ በተካሄደው በዓለም የድብልቅ ማርሻል አርት (ኤምኤምኤ) ከባድ ሚዛን ውድድር ካሜሩናዊው ፍራንሲስ ንጋኑ ብራዚላዊውን ፍሊፕ ሊንስ በመጀመሪያው ዙር ግጥሚያ በዝረራ አሸንፏል፡፡

ትናንት ምሽት በተካሄደው ውድድር ንጋኑ ከብራዚላዊው የኤምኤምኤ ኮከብ ፍሊፕ ሊንስ ከባድ ፉክክር ቢገጥመውም በሰነዘረው ቡጢ በዝረራ ማሸነፍ ችሏል።

ድሉ ካሜሮናዊው የኤምኤምኤ ኮከብ በአራት ዓመታት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ያሳካው ድል ሆኖ ተመዘግቦለታል፡፡

ፍራንሲስ ንጋኑ በቀጣይም ከአሜሪካዊያኑ ከባድ ሚዛን ቦክስ እና ኤምኤምኤ ተፋላሚዎቹ ጄክ ፖል እና ጆን ቦንስ ጋር ይጋጠማል፡፡

ፍራንሲስ ንጋኑ በፈረንጆቹ 2021 መጋቢት ወር ላይ በተካሄደ ውድድር በሁለተኛው ዙር ተጋጣሚውን በማሸነፍ የዓለም የከባድ ሚዛን ሻምፒዮን መሆኑ ይታወሳል፡፡

በሚኪያስ አየለ

Exit mobile version