አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ የሀሮማያ ሐይቅ ዳግም መወለድ አረንጓዴ አሻራ ከሰጠን ፍሬዎች አንዱ ነው አሉ፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥ አረንጓዴ አሻራ የተፈጥሮን ጉዳት እያከመ ለመሆኑ የሀሮማያ ሐይቅ ህያው ማሳያ ነው ብለዋል፡፡
በ1996 ዓ.ም ሙሉ በሙሉ ጠፍቶ የነበረው ሐይቁ በአረንጓዴ አሻራ እና በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ጥረት ዛሬ ወደ ቀደመ ውበትና ሥሪቱ ተመልሷል ነው ያሉት።
ይህም አረንጓዴ አሻራን ለኢትዮጵያ የውሃ አካላትና ለተፋሰስ ልማት ቁልፍ ኢኒሼቲቭነቱን በተግባር ያረጋገጠ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ይህ ስኬት በመደመር እሳቤ ልማትን ማረጋገጥ ብቻ ሳይሆን የተፈጥሮን ጫና መቋቋምና መግራት እንደሚቻል ማረጋገጫ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡

