Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

አዲስ አበባ እና ባኩ የእህትማማች ከተሞች ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አዲስ አበባ እና የአዘርባጃን ዋና ከተማ ባኩ የእህትማማች ከተሞች ስምምነት ተፈራርመዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳሉት፥ ስምምነቱ የሁለቱን ሀገራት ህዝቦች የባህልና የታሪክ ልውውጥ የሚያጠናክር ነው፡፡
በተጨማሪም በከተማ ልማት፣ በአገልግሎት ዲጂታላይዜሽን፣ በቤት ልማት፣ የስፖርት ቱሪዝምን ጨምሮ በቱሪዝም ልማት የሁለቱን ከተሞች ትብብር ያጠናክራል ነው ያሉት፡፡
Exit mobile version