አዲስ አበባ፣ ግንቦት 12፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ የከተማዋ አገልግሎት አሰጣጥን፣ የኑሮ ውድነት ጫናን ለመቀነስ፣ ገበያን ለማረጋጋት እና ለማረቅ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ገምግመዋል።
ከንቲባዋ በማሕበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት÷ ዛሬ ከሴክተር፣ ከክፍለ ከተማ እና ከወረዳ አመራሮች ጋር የአገልግሎት አሰጣጥን፣ የኑሮ ውድነት ጫናን ለመቀነስ፣ ገበያን ለማረጋጋት እና ለማረቅ የምንሰራውን ስራ ገምግመናል ብለዋል።
በመደበኛው አሰራርም ሆነ በመሶብ ዲጂታል የአንድ ማዕከል የአገልግሎት አሰጣጥ በታቀደው መሰረት እየተሻሻለ መሆኑን እና የኑሮ ውድነት ጫናን ለመቀነስ፣ ገበያን ለማረጋጋት እና ለማረቅ እየተሰራ ያለው ስራ በአብዛኛው ውጤታማ መሆኑን ገልጸዋል።
በነዳጅ ምክንያት ከፍ ያሉ የአንዳድ ሸቀጦች ዋጋዎች አሁንም በተሟላ ሁኔታ እንዳልወረዱ ተረድተናል ያሉት ከንቲባዋ÷ በመሆኑም አንዳንድ የማስተካከያ እርምጃዎችን መውሰዳችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።

