Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ሀገር አቀፍ የጸሎት መርሐ ግብር የፊታችን ግንቦት 16 ቀን ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የጸሎት መርሐ ግብር ይካሄዳል አለ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ፡፡

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ጸሀፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት÷ በሀገር ጉዳይ ላይ የአደባባይ የጸሎት መርሐ ግብር ይካሄዳል።

የጸሎት መርሐ ግብሩ ኢትዮጵያ የጀመረችውን የልማት ጉዞ አጠናክራ እንድትቀጥል፤ ብሔራዊ ጥቅማችን እንዲከበር እንዲሁም ሰላም እና አብሮነትን ለመገንባት ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል፡፡

ግንቦት 16 ቀን ዕለተ እሁድ ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ጀምሮ በአራዳ ፓርክ የጸሎት መርሐ ግብሩ እንደሚካሄድ ገልጸዋል።

በጸሎት መርሐ ግብሩ ላይ የሃይማኖት መሪዎች፣ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እና የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ተወካዮች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እንደሚገኙ ተመላክቷል፡፡

በቅድስት ብርሃኑ

Exit mobile version