Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ፈረንሳይ የኔቶ ጦር በሆርሙዝ ሰርጥ እንዲሰማራ የቀረበውን ሀሳብ ውድቅ አደረገች

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 13፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ፈረንሳይ የሰሜን አትላንቲክ የጦር ቃልኪዳን ድርጅት (ኔቶ) በሆርሙዝ ሰርጥ እንዲሰማራ ከአባል ሀገራቱ የቀረበውን ሀሳብ ውድቅ አድርጋለች፡፡

የኔቶ ጦር ህብረት ከፍተኛ አዛዥ የሆኑት ጄነራል አሌክስ ግሪንኬዊች ኔቶ የሆርሙዝ ሰርጥን ደህንነት ለመጠበቅ ሰራዊቱን በቀጣናው ለማሰማራት እያጤነ እንደሆነ ከቀናት በፊት ገልጸው ነበር፡፡

የፈረንሳይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፓስካል ኮንፋቭሬክስ እንደገለጹት÷ ስትራቴጂክ መተላለፊያ በሆነው የሆርሙዝ ሰርጥ የኔቶ ጦር እንቅስቃሴ እንዲያደርግ የቀረበውን ሀሳብ ፓሪስ አጥብቃ ትቃወመዋለች፡፡

የሆርሙዝ ሰርጥ የሚከፈተው በንግግር ብቻ ነው ያሉት ቃል አቀባዩ፥ ፈረንሳይ ሰርጡን በሰላማዊ መንገድ ለማስከፈት በሚደረገው ተልዕኮ ብቻ ትሳተፋለች ነው ያሉት፡፡

በሌላ በኩል እስራኤል እና ሂዝቦላህ የሌባኖስን የተኩስ አቁም ስምምነት በመጣስ በድጋሚ ወደ ግጭት መግባታቸው ተቀባይነት እንደሌለው ተናግረዋል፡፡

ሁለቱ ወገኖች አሁንም ወደ ቀጥታ ድርድር እንዲመጡና እያካሄዱ ባለው ግጭት ንጹሃን ዜጎችን እንዲጠብቁ ማሳሰባቸውን ቲ አር ቲ ወርልድ ዘግቧል፡፡

በሚኪያስ አየለ

Exit mobile version