አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አሜሪካ የ108 ነጥብ 1 ሚሊየን ዶላር የሚያወጡ የዩክሬንን አየር መከላከያ ሥርዓት የሚያጠናክሩ እና ተያያዥ የድጋፍ መሳሪያዎችን ለመሸጥ አጸደቀች።
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት እንዳስታወቀው÷ የወታደራዊ ቁሳቁስ ሽያጩ ኤችኤደብሊውኬ (HAWK) የተባለውን የዩክሬን የአየር መከላከያ ስርዓት የሚደግፍ ነው።
ስምምነቱ የጥገና፣ የመለዋወጫ እቃዎች፣ የምህንድስና እና የሎጂስቲክስ ድጋፍን ያካተተ መሆኑን ገልጿል።
ይህም የዩክሬንን የአየር መከላከል አቅምን ያጠናክራል መባሉን ኬይቭ ፖስት ዘግቧል።
እንዲሁም ሀገሪቱ ራሷን ለመከላከልና ለቀጣናው ደኅንነት ተልዕኮዎች ያላትን የተቀናጀ የአየር መከላከያ አቅም በማጠናከር ወቅታዊ እና የወደፊት ስጋቶቿን ለመፍታት እንደሚረዳ ተገልጿል።
በብርሃኑ አበራ

