አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ አጀንዳዎችን ለሃይማኖት ተቋማትና ለሲቪክ ማህበራት አቅርቧል፡፡
የኮሚሽኑ ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርዓያ (ፕ/ር)፤ ለሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የሚቀርቡ አጀንዳዎች ላይ ከሃይማኖት ተቋማትና ሲቪክ ማህበራት ጋር የማረጋገጥ ስራ መስራታችን የምክክሩን ተዓማኒነት ያሳድጋል ብለዋል፡፡
ኮሚሽኑ አጀንዳ የመቅረፅ፣ የማደራጀትና የማጠናቀር ምዕራፍ ላይ መሆኑን ጠቅሰው፤ በቀጣይ ለሀገራዊ ምክክር ጉባኤ የሚቀርቡ አጀንዳዎች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የማረጋገጫ ስራ እየሰራ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡
ኮሚሽኑ እየሰራ ያለውንና የቀረጸውን አጀንዳ ለሃይማኖት ተቋማትና ለሲቪክ ማህበራት አቅርቦ ግብዓት እየሰበሰበ ይገኛል።
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክትል ፕሬዚዳንት አህመድ ሁሴን በበኩላቸው የአጀንዳ ማረጋገጫ ስራ ለቀጣይ ውይይቶቻችን መሰረት የሚጥል ወሳኝ እርምጃ ነው ብለዋል።
የተመረጡት አጀንዳዎች የዜጎች እውነተኛ ጥያቄዎች ላይ የተመሰረቱ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ የሴቶች፣ ወጣቶች እና አካል ጉዳተኞችን ጨምሮ የሁሉንም ማህበረሰብ ጥያቄ ይመልሳል ነው ያሉት፡፡
በዓለምሰገድ አሳዬ

