አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) ባለፉት አምስት ዓመታት የተከናወኑ የልማት አሻራዎች የኢትዮጵያን ብልጽግና አይቀሬነት ይመሰክራሉ አሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ።
ከንቲባዋ “ወጣት ይምረጥ ኢትዮጵያ ትጽና” በሚል መሪ ሃሳብ በገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከከተማዋ ወጣቶች ጋር የምርጫ ቅስቀሳ መርሐ ግብር አካሂደዋል።
ከንቲባ አዳነች በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ስለ ወጣቱ ተጠቃሚነት ችግር ከማውራት ይልቅ በቀን 24 ሰዓት በሳምንት 7 ቀናት በመስራት ለችግሩ ተግባራዊ ምላሽ ለመስጠት እየተሰራ ነው፡፡
የወጣቱ ተጠቃሚነት ከተረጋገጠባቸው ስፍራዎች አንዱ በሆነው በገላን ጉራ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከ70 ሺህ በላይ ከሆኑ የከተማዋ ወጣቶች ጋር በስፖርታዊ እንቅስቃሴ የምርጫ ቅስቀሳ ማካሄዳቸውን ጠቁመዋል።
ባለፉት 5 ዓመታት የሰራናቸው የልማት አሻራዎች የኢትዮጵያን ብልጽግና አይቀሬነት ይመሰክራሉ ያሉት ከንቲባዋ÷ ከማንም በላይ ሀገር እየተገነባች ያለችው ለወጣቶች መሆኑን አመልክተዋል።
የከተማዋ ወጣቶች የብልጽግና ፓርቲን ራዕይ፣ የወደፊት አሻራ፣ ሁለንተናዊ እድገት በመሰነቅና ያለውን ተስፋ በመጋራት ላሳዩት ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

