አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በሰሜናዊ ቻይና ሻንሺ ግዛት በሚገኝ የድንጋይ ከሰል ማዕድን ማጣሪያ ማዕከል ላይ በደረሰ የጋዝ ፍንዳታ ቢያንስ የ90 ሰዎች ሕይወት አልፏል፡፡
አደጋው በቶንግዡ ግሩፕ በሚተዳደረው ሊውሼንዩ የድንጋይ ከሰል ማዕድን ማጣሪያ ማዕከል ውስጥ የተከሰተ ሲሆን ÷ ፍንዳታው በደረሰበት ወቅት 247 ሰራተኞች በሥራ ላይ እንደነበሩ ተመላክቷል፡፡
ክስተቱን ተከትሎ 345 ባለሙያዎችን ያካተተ የነፍስ አድን ልዑክ እና በርካታ አምቡላንሶች በሥፍራው መሰማራታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
የቻይናው ፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ÷ ለተጎጂዎች ፈጣን ሕክምና እንዲደረግና በሕይወት የተረፉ ሰዎችን ለመፈለግ የሚደረገው ርብርብ በሙሉ አቅም ተጠናክሮ እንዲቀጥል አሳስበዋል፡፡
በድንጋይ ከሰል ማጣሪያ ማዕከሉ ላይ የተፈጠረውን ፍንዳታ ትክክለኛ መንስኤ ለማጣራት ምርመራ መጀመሩንም አመልክተዋል፡፡
በሶስና አለማየሁ

