አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የጣሊያኑ ክለብ ኤሲሚላን ከአሰልጣኝ ማሲሚሊያኖ አሌግሪ ጋር ተለያይቷል፡፡
ሚላን በሴሪ ኤው የውድድር ዓመቱ የመጨረሻ ጨዋታ በካግሊያሪ 2 ለ 1 መሸነፉን ተከትሎ 5ኛ ደረጃን ይዞ ለማጠናቀቅ ተገዷል፡፡
በዚህም በተከታታይ ሁለት ዓመታት የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ቦታን ማግኘት ሳይችል ቀርቷል፡፡
ክለቡ ለአሰልጣኙ መሰናበት የውጤት ቀውስን ምክንያት አድርጓል፡፡
ኢንተር ሚላን፣ ናፖሊ፣ ሮማ እና ኮሞ ጣሊያንን በመወከል በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ መድረክ በቀጣይ የውድድር ዘመን ይጫወታሉ።

