Site icon Welcome to Fana Media Corporation S.C

ያላ የወተት ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ለግዙፍ አግሮ ኢንዱስትሪዎች መስፋፋት በር ከፋች ነው – አቶ ጥላሁን ከበደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ጥላሁን ከበደ በጋሞ ዞን የተገነባውን ያላ የወተት ማቀነባበሪያ ፋብሪካ በዛሬው ዕለት መርቀው ከፍተዋል።
ርዕሰ መስተደድሩ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፥ ፋብሪካው ለአካባቢው አርሶ አደሮችና ወጣቶች አስተማማኝ የገበያ ትስስር በመፍጠር ረገድ ከፍተኛ አበርክቶ ይኖረዋል።
የግብርና ምርትን በማስፋት ኢንዱስትሪያላይዜሽንን ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት ያላ የወተት ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ለቀጣይ ግዙፍ የአግሮ ኢንዱስትሪዎች በር ከፋች ነው ብለዋል።
በቀጣይ በሁሉም የክልሉ አካባቢዎች የወተት ላሞችን በስፋት በማቅረብ የወተት አቅርቦት ሰንሰለትን ማረጋገጥ የሚያስችሉ አርሶ አደሮችን እንፈጥራለን ነው ያሉት፡፡
ያላ የወተት ማቀነባበሪያ ፋብሪካ ከ5 ሺህ በላይ አርሶ አደሮችን በቀጥታ የእሴት ሰንሰለት ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን፥ ለአርሶ አደሩ አስተማማኝ የገበያ እድል ለመፍጠር መሰል ፋብሪካዎችን ማስፋት እንደሚገባ አፅንኦት ሰጥተዋል።
ፋብሪካው በቀን ከ8 ሺህ ሊትር በላይ ወተት የማምረት እስከ 24 ሺህ ሊትር ወተት የማቀነባበር አቅም እንዳለው ተገልጿል፡፡
በዓለምሰገድ አሳዬ
Exit mobile version